Mezmur Wiki
Advertisement
ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

"ወይ የመታልፍ ብሎ ያለወትሮው ሞልቶ ዮርዳኖስ ቢፎክር ብቆመም ከፊቴ

በዳር አስከክብር እሄዳለሁ አልፈራም ጌታ ነው ጉልበቴ

ረግጬው አልፋለሁ ጌታ ነው ጉልበቴ ፣ እየሱስ ነው ጉልበቴ"


[ቢጮህም አያሸንፍም ፣ ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ፣ ለጠላት ዕድል አልሰጠው] /፪

[ለጠላት ዕድል አልሰጠው] /፬


[ሰባት እጥፍ ብያነድ ጠላቴ ፣ እሳቱን አብዝቶ

ከከፍታዬ ላይ አልወርድም ፣ ስፍራ አለቅም ከቶ

የመቆሜ ሚስጥር ጌታ እንጂ ፣ አይደለም ሁኔታ

የታመንኩበትን አውቃለሁ ፣ አንደማይረታ] /፪


[ቢጮህም አያሸንፍም ፣ ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ፣ ለጠላት ዕድል አልሰጠው] /፪

[ለጠላት ዕድል አልሰጠው] /፬


ጠላቴን ከፊቴ አውጥቶት ፣ አጥፋው ብሎ አዞኛል

አስጨናቂውን ዘንግ ጌታ ፣ ፈጥኖ ሰብሮልኛል

የከፍተኛነቴ ሰይፍ ፣ ብቃቴም እርሱ ነው

አትፍራ ሰላለኝ አልፈራም ፣ ጌታ ከኔ ጋር ነው

[ጌታ ከኔ ጋር ነው] /፬


[ቢጮህም አያሸንፍም ፣ ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ፣ ለጠላት ዕድል አልሰጠው] /፪

[ለጠላት ዕድል አልሰጠው] /፬


[ ከትላንቱ ይልቅ [ዛሬ አስደንቆኛል] /፪

እግዚአብሔር ስራዬን [ሁሉ ሰርቶልናል] /፪

ላመስግነው አንጂ [ስሙን በዝማሬ] /፪

ለጠላቴ ሃዘን [የድል ቀን ነው ዛሬ] /፪ ] /2


[ቢጮህም አያሸንፍም ፣ ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም

የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ፣ ለጠላት ዕድል አልሰጠው] /፪

ለጠላት ዕድል አልሰጠው /፱

am.mezmur.wikia.com wikimezmur.org Amharic Mezmur thumb|400px|left|ፓስተር ካሳሁን ለማ - ከልኩ አያልፍም ( Pastor Kassahun Lemma - keleku Ayalfem )

Advertisement