FANDOM


ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

ሳይሳሱ ፍቅሩን ወግተው ፣ ውርደት አለበሱት

ስለፈወሳት ብለው ፣ ባፈቀረ ጠሉት

የድሃ አዛኝ የሆንከው ፣ አንተ ነህ እየሱስ

ይገባ ነበረ ወይ ፣ ለኔ ያ??? ነፍስ


[የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ የሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና] /፫


አንተ ፍቅር ነህና ፣ ልትጠላኝ አቃተህ

ነፍሴን ከእሳት አወጣህ ፣ እራስህን ጎድተህ

የኔ የሆነ ምን አለኝ ፣ እራሴም ያንተው ነኝ

ስለዚህ ጌታዬ ሆይ ፣ ደጋግመህ አምልጠኝ


[የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ የሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና] /፪


ኑሮዬና ተግባሬ ፣ ለኔ ባይጥመኝም

ጠላቴ እየወጋን ቢያደናቅፈኝም

አንድ ጊዜ ቆርጬ ተከትየሃለሁ

ድካም እንኳ ቢያጠቃኝ እከተልሃለሁ


[የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ የሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና] /፪


ያየምድር ጨለማ ፣ አይሎ እንዳይውጠኝ

መንፈስ ቅዱስ ጌታዬ ሳጠፋ ገስጸኝ

መምበርከክም ይበጃል ስጋ ላለም ነገር

ጽናትን እሻለሁ ከቶ እንዳልቀየር


[የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ የሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና] /፪

am.mezmur.wikia.com

wikimezmur.org

thumb|400px|left|አዲሱ ወርቁ - የእግዚአብሔር በግ ( Addisu Worku - Ye Igziabhare Beg )