ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ። This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit. |
ቤተልሔም ተዘራ : ተሳልሜ አልሄድም (Bethlehem Tezera - Tesal'me Alhedim)
አነጋልኝ : ዛሬን : [በዕድሜዬ : ጨመረው] /፪
በስሙ : ዋጅቼ : [ቀኑን : ልጀምረው] /፪
አይ : አይ : አይ : ሳላመልክ : በከንቱ : አይ
አይለፍ : ዕለቱ : አይ : አይ : አይ::
አምልኪው : ተብዬ : ተነግሮኝ : ጀምሬ
አምልኩት : እላለሁ : እኔ : ደግሞ : ዛሬ
አምልኪው : አምልኪው : ተብዬ : ጀምሬ
አምልኩት : እላለሁ : እኔ : ደግሞ : ዛሬ
እናም : እግዚአብሔር : የሚመለከው
ጠጋ : ተብሎ : ነው
እናም : እግዚአብሔር : የሚመለከው
በእውነት : በመንፈስ : ነው ::
{ማደሪያው : ሥር : እሆናለው : እንጂ
ዙፋኑ : ሥር : እሰግዳለሁ : እንጂ
[ተሳልሜ : አልሄድም : ከደጅ] /፬ } /፪
ሃያ : አራቱ : ሽማግሌዎች : ቅዱስ : ቅዱስ
እልፍ : አእላፍ : መላእክቱ : ቅዱስ : ቅዱስ
ምስጋናም : አለው : የተረፈ
ከእኔ : የሚሻው : ከቃሌ : ባለፈ
አምላክ : አለው : የተረፈ
እኔም : ልዘምር : ከቃሌ : ባለፈ /፪
[ሰው : በከንፈሩ : አምልኮ
ልቡን : ከእግዚአብሔር : ቢያርቀው
ልብን : የሚመረምረው
የአፉን : ቃል : ብቻ : አይሰማው]/፪
{ማደሪያው : ሥር : እሆናለው : እንጂ
ዙፋኑ : ሥር : እሰግዳለሁ : እንጂ
[ተሳልሜ : አልሄድም : ከደጅ] /፬ } /፪
[ለልቤ ጌታ ከልቤ
ለልቤ ንጉስ ከልቤ
እስቲ ልዘምር ከልቤ
ዛሬም እንደ ልጅነቴ] /፪
{ [እኔ ያመንኩትን አውቃለሁን
ልንገረው የሚሻ] /፪
ጌታ ነው የመጀመሪያ
ጌታ ነው የመጨረሻ
አምላክ ነው የመጀመሪያ
አምላክ ነው የመጨረሻ } /2
ኃይለኛ : የመጀመሪያ
ኃይለኛ : የመጨረሻ
ታዋቂ : ነው : የመጀመሪያ
ታዋቂ : ነው : የመጨረሻ
ዝነኛ : ነው : የመጀመሪያ
ዝነኛ : ነው : የመጨረሻ
ንጉስ : ነው : የመጀመሪያ
ንጉስ : ነው : የመጨረሻ
ጌታ : ነው : የመጀመሪያ
ጌታ : ነው : ነው : የመጨረሻ
አምላክ : ነው : የመጀመሪያ
አምላክ : ነው : የመጨረሻ መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:ቤተልሔም (ቤቲ) ተዘራ ( Bethlehem (Betty) Tezera) መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:ቤተልሔም (ቤቲ) ተዘራ ( Bethlehem (Betty) Tezera)